Fair play by Ivan Fernandez Anaya

20.01.2013
fair play on Spain Burlada cross country held on Dec 2 2012 Ivan Fernandez show his revival Abel Mutai what it means fair play practically. በዴሴምበር 2, 2012 እ.ኤ.አ በስፔን ቡርላዳ በተከናወነው የአገር አቋራጭ ውድድር ላይ የታየው ያልተለመደ ክስተት ነበር :: በዕለቱ ውድድሩን በበላይነት ተቆጣጥሮ ሲመራ የቆየው በለንደን ኦሎምፒክ 3000 ሜትር መሰናክል የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ የነበረው ኬንያዊ አቤል ሙታይ ነበር:: ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ አናያ በቅርብ ርቀት በሁለተኛነት እየተከተለ የተቻለውን ሁሉ እናደረገ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል:: ውድድሩ ወደማለቂያው ተቃርቧል የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ሜትሮች ናቸው ኬንያዊው ሙታይ የውድድር ማብቂያውን መስመርና ገመድ በ10 ሜትር ያልቀረ ዕርቀት ላይ ሲደርስ በሙሉ ልብ አሸንፌያለሁ በሚል ኩራት ፍጥነቱን ቀንሶ በተረጋጋ ሁኔታ ወደመስመሩ ሳይደርስ በሁለተኛነት የሚከተለው ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ አናያ ፍጥነቱን ጨምሮ ተፈትለኮ ከፊት ሲመራው የቆየው ሙታይ ላይ ይደርስበታል ፣ በቦታው የተገኙ ስፔናዊ ታዳሚዎች በጉጉት አልፎ አሸነፈው ብለው በከፍተኛ ጩኸት ሲያጅቡት ኢቫን ፈርናንዴዝ አናያ ያደረገው ግን ለብዙኻኑ አስገራሚ የሆነ ነው:: ተፎካካሪውን ሙታይን አልፎ ከማሸነፍ ይልቅ እርስዎ ከፊትዎ ያለ ጓደኛዎን ዞር ብሎ እንዲያይዎ የሚጠሩበትን አይነት በጣትዎ ትከሻውን ነካ አድርገው እንደሚያዞሩት አይነት አጠራር ትከሻውን ነካ አድርጎ ይነካውና እየኝ መጥቻለሁ ፍጥነትህን ጭመር አድርገና ገባ የሚል መልዕክ አዘል ምልክት ያሳየዋል ሙታይም ሲለፋ የቆየበት ውድድር ነው እና አመስግኖ ገመዱን በጥሶ ገባ:: ከውድድሩ በኋላ ሲጠየቅ ኢቫን ፈርናንዴዝ አናያ ለምን አላለፍከውም ማሸነፍ አትፈልገም እንዴ ተብሎ ሲጠየቅ :: አይ ሙታይ ብዙ ለፍቶዐል ማሸነፍ ለሱ ነው የሚገባው ባደረገው ጥቂት ስህተት የልፋቱን ውጤት ማጣት የለበትም ብሎዐል:: ባደረኩት አልፀፀትም ትክክል ነበርኩ የእውነተኝነት እጅ ምልክት ነበር ብሏል:: ካሁን ቀደም ያልነበር እኔ ያሳየሁት የእጅ ምልክት ነው ብሏል:: እኤአ በ1997 የደረሰበትን እያስታወሰ በአቴንስ አለም አቀፍ አትሌቲክስ አለም ዋንጫ ላይ በሀገሩ ልጅ የደረሰበትን እያስታወሰ ውድድሩ ላይ ሙሉውን ከሀገሩ ልጅ አቤል አንቶን ፊት ፊት ሲሮጥ ይቆይና ማጠናቀቂያው መስመር ላይ ሊደርሱ ያገሩ ልጅ የሆነው አቤል አልፎ አሸነፈው በዚያ በጣም የተበሳጨው ኢቫን ፈርናንዴዝ በሱ ላይ የደረሰው ብስጭት በሙታይ ላይ መድገምና መፀፀት አልፈለገም ::ስፖርታው ጨዋነት ይሎታል ይሄ ነው!!! http://mikililand.wordpress.com/

Похожие видео

Показать еще